በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶርያን የዒድሊብ ክልልን የማስመለስ ዕቅድ ሩስያ ደገፈች

ሶርያ በአማጽያን ቁጥጥር ሥር ያለውን የዒድሊብ ክልልን ለማስመለስ ማቀዷን ሩስያ ዛሬ ድጋፍዋን ገልፃለች። ኢራንም ትላንት የድጋፍ ድምፅ አስምታ ነበር። የመጨረሻው በአማፅያን ቁጥጥር ሥር ያለ ክልል ነው።

ሶርያ በአማጽያን ቁጥጥር ሥር ያለውን የዒድሊብ ክልልን ለማስመለስ ማቀዷን ሩስያ ዛሬ ድጋፍዋን ገልፃለች። ኢራንም ትላንት የድጋፍ ድምፅ አስምታ ነበር። የመጨረሻው በአማፅያን ቁጥጥር ሥር ያለ ክልል ነው።

የክርምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮፍ ዒድሊብ የአሸባሪነት ሰፈር ነው። የሶርያው ግጭት የፖለቲካ መፍትሄ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት ያወጣው መግለጫም ዒድሊብ ከአሸባሪዎች ነፃ መሆን አለበት ይላል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ ትላንት ሶርያን በጎበኙበት ወቅት ዒድሊብ ወደ ሶርያ ሕዝብ ቁጥጥር መመለስ ይኖርባታል። የመልሶ ግንባታ ተግባርና የሰደተኞች መመለስም መቀጠል አለበት ሲሉ ዛሪፍ መናገራቸውን የኢራን ሚድያ ጠቅሷል።

ዒድሊብ ውስጥ ሦስት ሚልዮን ህዝብ ይኖራል። ሶርያ በክልሉ ወታደራዊ ጥቃት ብትከፍት ሊከተል የሚችለው ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያሳስበው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG