በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የኮቪድ-19 አዲስ መመሪያ ወጣ


የሩስያ ባለሥልጣናት በመላ ሃገሪቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀምን ግዴታ የሚያደርግ መመሪያ አውጥተዋል።

የሩስያ መንግሥት ይህን እርምጃ የወሰደው በሃገሪቱ በአንድ ቀን ከምንጊዜውም የበዛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ በሞቱበት እና የቫይረሱ ሥርጭትም እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው።

በሩስያ ዛሬ ብቻ ሦስት መቶ ሃያ ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሞተዋል።

ወረርሽኙ ሃገሪቱ ውስጥ ከገባ ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቁ ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም በዛሬው ዕለት 16550 አዲስ የቫይረሱ ተያዥች ተመዝግበዋል።

ሩስያ ውስጥ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ሰው በሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ በህዝብ ማጓጓዣዎች፣በታክሲዎች እንዲሁም በፎቅ መውጫ ኤሌቪተሮች ውስጥ በጭንብል ፊትን መሸፈን ግዴታ መሆኑ ታውጇል።

ከዚህም ሌላ ምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ከማታው አምስት እስከ ንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት እንዲዘጉ ታዟል።

XS
SM
MD
LG