በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰባ አንድ ሰዎችን እንደያዘ የጠፋው የሩስያ አውሮፕላን ፍለጋ ቀጥሏል

ትናንት ሰባ አንድ ሰዎችን እንደያዘ የደረሰበት የጠፋውን የሩስያ አውሮፕላን ፍለጋ ቀጥሏል። ስድሥቱ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሲሆኑ ሥልሳ አምስቱ ግን፣ ከ5-79 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መንገደኞች እንደነበሩም ታውቋል።

ትናንት ሰባ አንድ ሰዎችን እንደያዘ የደረሰበት የጠፋውን የሩስያ አውሮፕላን ፍለጋ ቀጥሏል። ስድሥቱ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሲሆኑ ሥልሳ አምስቱ ግን፣ ከ5-79 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መንገደኞች እንደነበሩም ታውቋል።

በዛሬው ፍለጋ 4መቶ ሰዎችና ሰባ ተሽከርካሪዎች የተሰማሩ መሆናችን፣ የሩስያ አስቸኳይ ጊዜ መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

የዚህን አንቶኖቭ ኤኤን 48 አውሮፕላን አደጋ ለማጣራትና ምርመራ ለማካሄድ፣ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አንድ ልዩ ኮሚሽን እንዲቋቋም አድርገዋል።

አደጋው ከሽብርተኛነት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ምንም ያልገለጸው የሩስያው መርማሪ ኮሚቴ፣ እንደ ሰበብ የሰጠው ምክንያት ቢኖር የሰው ስህተት፣ መጥፎ የአየር ሁኔታና የቴክኒክ ስህተት የሚሉ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG