በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሩስያ የዩናይትድ ስቴትስን የፖለቲካ መድረክ ማተራመስ ተሳክቶላታል"- ፕሬዚዳንት ትረምፕ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ሩስያ የዩናይትድ ስቴትስን የፖለቲካ መድረክ ማተራመስ በደምብ አድርጎ ተሳክቶላታል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ፡፡

ሩስያ የዩናይትድ ስቴትስን የፖለቲካ መድረክ ማተራመስ በደምብ አድርጎ ተሳክቶላታል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ፡፡

ሩስያ በአምናው ምርጫ ጣልቃ በመግባትዋ ጉዳይ ለወራት የቀጠሉት ምርመራዎች ፖለቲካውን ማተራመሱን እጅግ በጣም እንዳሳካላት አምናለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በትዊተር በፃፉት አስተያየት የሩስያ ዓላማ ዩናይትድ ስቴትስን ማናጋት፣ ማጣላት፣ መበጥበጥ ከሆነ ይሄ ሁሉ የኮንግረስ ኮሚቴ ምርመራ እና በሪፖብሊካን ፓርቲው ላይ ያለው ጥላቻ ዓላማቸውን ካለሙት በላይ አሳክቶላቸዋል ብለዋል። አያይዘውም ሞስኮ ውስጥ እየሳቁብን ነው እንወቅበት ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG