ዋሺንግተን ዲሲ —
ኮሎኮልሰፍ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጋዜጠኛውን ያሰረው ፖሊስ ከሥራ መታገዱን ገልፀዋል። ኢቫን ጋሉኖቭ ላይ የተደረገው የአሻራ፣ የሥነ ፍጥረታዊ፣ የወንጀልና የዘረመል ምርመራ በወንጀል ተግባር መሰማራቱን የሚያሳይ ማስረጃ ስላላሳዩ ክሱ እንዲነሳ ተደርጓል ብለዋል።
“ዛሬ ከቁም እስርነት ይለቀቃል፣ የተመሰረተበት ክስም ይሰረዛል” ብለዋል ባለሥልጣኑ በሰጡት መግለጫ። የእስራቱ ህጋዊነት ላይም የውስጥ ምርመራ ይደረጋል ተብሏል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ