በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዛሬው የድል በዓሏ ኪየቭ ላይ የሚሳይል ጥቃት አደረሰች


በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የተጎዳ ህንፃ ፣በዲኒፕሮ፤ ዩክሬን
በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የተጎዳ ህንፃ ፣በዲኒፕሮ፤ ዩክሬን

"ዓለም ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች" ያሉት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን "ሩሲያ በተጨባጭ ጦርነት ተከፍቶባታል" ሲሉ ተናገሩ።

ፑቲን ይህን ያሉት ዛሬ በሞስኮ በተከበረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመን ድል የተደረገችበት መታሰቢያ ላይ ባሰሙት ንግግር ላይ ነው። በሩሲያ ትልቅ ዓዐል በሆነው በዚህ የድል ቀን መታሰቢያ በሞስኮ ቀዩ አደባባይ ላይ የተካሄደው የወታደራዊ ሰልፍ ትዕይንት ለመመልከት ብዙ ሺህ ሰዎች ታድመዋል።

"ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን መክተን መልሰናል" ያሉት የሩሲያው ፕሬዚዳንት የዶንባስን ነዋሪዎች ደህንነት እንጠብቃቸዋለን፥ ጸጥታችንን እናስከብራለን" ብለዋል።

በወታደራዊ ሰልፍ ትዕይንቱ ላይ የስድስት የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ሪፐብሊኮች መሪዎች ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር አብረው ተገኝተዋል።

ቢያንስ ሃያ የሚሆኑ የሩሲያ ከተሞች በዝርዝር ባልገለጹት "የጸጥታ ሥጋት" ምክንያት የድል በዐል አከባበሩን መሰረዛቸው ወይም አነስ ባለ መንገድ ማክበራቸው ተገልጿል። ሥጋታቸው ባለፈው ሳምንት "ዩክሬን ፕሬዚዳንቱን ለመግደል ክሬምሊን ቤተ መንግሥት ላይ የድሮን ጥቃት ሙከራ አድርጋለች " ከሚለው የሞስኮ ውንጀላ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ተመልክቷል። ዩክሬን ውንጀላውን አስተባብላለች።

ከፑቲን ንግግር በሰዓታት ቀደም ብሎ የሩስያ ኃይሎች የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ብዛት ያለው ሚሳይል መተኮሳቸው ተዘግቧል።

በተያያዘ ዜና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሊዮን ዛሬ ኪየቭን የጎበኙ ሲሆን የአውሮፓ ሀገሮች ለዩክሬን ያላቸው ድጋፍ የጸና መሆኑን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG