በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በአንድ ቀን 5ሺህ የተቃውሞ ሰልፈኞችን አሰረች


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰውን ጥቃት በመቃወም የወጡ ሰልፈኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል፤ ሴንት ፒተርስበርግ፣ ሩሲያ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰውን ጥቃት በመቃወም የወጡ ሰልፈኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል፤ ሴንት ፒተርስበርግ፣ ሩሲያ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ የሚያደርጉትን ጥቃት በመቃወሙ ትናንት እሁድ በበርካታ ከተሞች አደባባይ ከወጡ ሩሲያውያን ውስጥ ከ5ሺህ በላይ የሚሆኑትን በቁጥጥር ስር በማዋል ክሬምሊን በዩክሬይኑ ወታደራዊ ዘመቻ ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞዎች ለመቆጣጠር የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሯል።

በተቃውሞው ወቅት የሚፈጸሙ እስራቶችን የሚከታተለው 'ኦቪዲ-ኢንፎ' የተባለው እና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ዘገባዎች የሚያቀርበው የሩሲያ ገለልተኛ የሚዲያ ፕሮጀክት እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት በ60 የተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች ከተሳተፉት ውስጥ ቁጥራቸው 5,016 የሚደርሱ የተቃውሞ ሰልፈኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።

በቡድኑ ዘገባ መሰረትም ከዚህ ውስጥ 2,394ቱ የታሰሩት ሞስኮ ውስጥ ሲሆን፤ በቅዱስ ፒተርስበርግም 1,253 ሰዎች ታስረዋል።

ይህ አሃዝ በዚያች አገር በአንድ ቀን ውስጥ በተፈጸሙ እስራቶች ታይቶ የማይታወቅ እና ባለፈው ዓመት የተቃዋሚ መሪው አሌክሲ ናቫልኒ በታሰረበት ወቅት በሃገሪቱ በተቀሰቀሰው የተቃውሞ ማዕበል ወቅት ከተፈጸሙት እስራቶችም በእጅጉ የላቀ መሆኑ ተዘግቧል።

በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ትናንሽ ከተሞች ውስጥም የተቃውሞ ሰልፎቹ ተካሂደዋል።

በተያያዘ ሌላ ዜና የተቃዋሚ መሪው ናቫልኒ ከእስር ቤት ክፍሉ ሆኖ ባሰማው ጥሪ ሩሲያውያን ጦርነቱን እንዲቃወሙ ጠይቋል።

በርካታ የመብት ሙግት አደራጆች እና አንቂዎች በእስራቶች እርምጃዎቹ ወቅት በፖሊስ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃችን የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎችን በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ አሰራጭተዋል።በተያያዘ ፖሊሶች የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚፈጥሩ መሳሪያዎችንም በሰልፈኞች ላይ ተጠቅመዋል ሲል ኦቪዲ-ኢንፎ ዘግቧል።

የተቃውሞ አድራዎች የእስር ቅጣት እንደሚጠብቅቸው የሚጠቁሙ የባለስልጣናት ማስጠንቀቂያዎች ቢሰሙም የፀረ-ጦርነት ተቃውሞዎቹ ግን አልተቋረጡም።

በክሬሚልን ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን ለማፈን የተደረገ ነው በተባለ እርምጃ የሩሲያ ጦር ኃይሎችን የተመለከተ የሃሰት ዘገባ ማሰራጨት እስከ 15 ዓመት የሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ ሕግ ፑቲን ባለፈው አርብ ፈርመው አጽድቀዋል።

XS
SM
MD
LG