በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያና ቻይና በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ ሥምምነት ተፈራረሙ


የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁአ ቹያንግ
የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁአ ቹያንግ

ሰሜን ኮሪያ የደቀነችው የሚሳይልና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ስጋት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ሩስያና ቻይና ያላቸውን ፍላጎት የሚገልፁ ሥምምነት ዛሬ ሰኞ መፈራረማቸው ተነገረ።

ሰሜን ኮሪያ የደቀነችው የሚሳይልና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ስጋት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ሩስያና ቻይና ያላቸውን ፍላጎት የሚገልፁ ሥምምነት ዛሬ ሰኞ መፈራረማቸው ተነገረ።

የሩስያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለመንግሥታዊው ዜና አውታር በሰጡት መግለጫ፣ በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት አካባቢ ጦርነት እንዲቀሰቀስ የሚፈልግ ማንም እንደሌለ ጠቁመው፣ ዩናይትድ ስቴትስም ብትሆን ውጥረቱን በጦር መሣሪያ ለመፍታት እንደማታቅድ አመልክተዋል።

የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁአ ቹያንግ በዛሬ የሰኞ ገለጻቸው፣ ሁሉም አገሮች ከጠብ ጫሪነት ተቆጥበው፣ በባሕረ ገቡ መሬት አካባቢ የተነሳው ውጥረት የሚረግብበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የተመድ የጣለው ማዕቀብም ቢሆን፣ የሰሜን ኮሪያን የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የሚያደናቅፍ መሆን እንደሌለበት ቻይና በአፅንዖት አመልክታለች።

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ባለፈው ዐርብ ወደ ሰሜን ኮሪያ ወዳገሯ የምታስገባውን የነዳጅና የናፍጣ አቅርቦት የሚገድብ ማዕቀብ በሙሉ ድምፅ ማሳለፉ አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG