በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ በአፍሪካ


የሩስያ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን
የሩስያ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን

የዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ መርማሪ ካውንስል ሮበርት ሞለር ባለፈው ዓመት በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካ እጃቸውን ዶለዋል በሚል የጠቅሷቸው የሩስያ ወታደርዊ ተቋራጭ የክረምሌን ተፅዕኖን በአፍሪካ ላይ ለማስፈን በሚያደርጉት ጥረት ቁልፍ ሰው ሆነው እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል።

ሩስያ በአፍሪካ ላይ የሚኖራትን ቦታ ለማጠናከር የሚያስችል ሰፊ አድማስ ያለው የክረምሊን ተፅዕኖ አሳዳሪ እንቅስቃሴ እየካሄዱ ናቸው ይላል በአንድ መርማሪ ቡድን የተገኘ ሰነድ። የምርመራ ጥናት እንዲካሄድ በገንዘብ የረዱት በውጭ ሃገር የሚኖሩ የሩስያውን መሪ ቭላዲሚር ፑቲንን የሚቃወሙ ናቸው።

የሩስያ መንግሥት የሚፈልጋቸውን ዓይነት ኩንትራት በማከናወን የሚታወቁት የ57 ዓመት ዕድሜ ይቭጌኒ ፕሪጎዥን ሩስያ ከሰሀራ በመለስ ባሉት የአፍሪካ ሃገሮች የስትራተጂ ማዕከል እንድትሆንና በአፍሪካ የምዕራቡ ዓለም ተፅዕኖ እንዲቀንስ ጥረት እያደረጉ ናቸው ተብሏል።

መጀመርያ ላይ ስለ ተባሉት ሰነዶች የዘገበው የብሪታንያው ጋርዲያን ጋዜጣ ነበር። የዋግነር ቡድን የተባለው ወታደራዊ ተቋራጭ በአፍሪካ ሃገሮች ስለሚካሂደው እንቅስቃሴና ስለ ዓላማው በዝርዝር ገልፆ ነበር። ዋግነር ቡድን የሩስያ መንግሥት ሶርያንና ኡክራይንን ለመሳሰሉት ወዳኞቹ ሀገሮች ሩስያውያን ቅጥረኞችን ያቀርባል ተብሏል። ኑሯቸው ፒተርስበርግ ከተማ የሆነው ፕሪጎዢን ዋግነር የሚባል ቡድን የለም ሲሉ ከዚህ ቀደም አስተባብለው ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG