በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የዩክሬንን ጦርነት እንዲቆም እንድትረዳ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ጥሪ አቀረቡ


የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የቻይናው አቻቸው ሺጂንፒንግ ከሩሲያ ጋራ ያላቸውን ግንኙነት ተጠቅመው በዩክሬን ላይ የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆ እንዲሠሩበት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዛሬ ሐሙስ ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጋራ ቤጂንግ ውስጥ ውይይት ያደረጉት ማክሮን፤ የዓለም ሰላም ሩሲያ ዩክሬን ላይ በከፈተችው ወረራ ምክኒያት መናጋቱ በማስታወስ ሺ አሳስበዋቸዋል፡፡

“ሩሲያ አስተሳሰቧን እንድትለውጥ እና ኹሉም ወገኖች ለድርድር እንዲቀመጡ እንደሚያደርጉ ልተማመንብዎት እንደምችል አውቃለሁ” ብለዋል ማክሮን፡፡

ቻይና ለዩክሬኑ ጦርነት ብዙ ክፍል ያለው የሰላም ዕቅድ አዘጋጅታለች፡፡ የሁሉም አገሮች ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር ጥሪ የሚያቀርበው የቻይናው ዕቅድ ሩሲያ ኃይሎቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ አይጠይቅም፡፡

የዩክሬን ባለሥልጣናት ሩሲያ የጦር ኃይሏን ሳታስወጣ የሰላም ድርድር ውስጥ እንደማይገቡ ሲያስታውቁ ቆይተዋል፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ግዛቶቼ ለምትላቸው አካባቢዎች ዩክሬን ዕውቅና እንድትሰጥ ጠይቃለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ትናንት ረቡዕ አጎራባች ፖላንድን የጎበኙ ሲሆን ስለጦርነቱ ወቅታዊ ይዞታ በዚያ ለሚገኙ መሪዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ ጦርነቱን ሸሽተው ፖላንድ የተጠለሉ ስደተኞችንም ጎብኝተዋል፡፡

የምስራቅ ዩክሬን ባኽሙት ሁኔታ ለዩክሬን ኃይሎች አሁንም አስቸጋሪ መሆኑን አስረድተው ወታደሮቹ በሩሲያ ኃይሎች ከተከበቡ አስፈላጊው ውሳኔ መወሰድ ይኖርበታል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG