በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬይን በዩናይትድ ስቴትስ ለተወጠነው የሰላም ንግግር ዕቅድ ልታቀርብ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ፣ የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪ ሲቢሃ፣ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንድሬ የርማክ; ጄዳ፣ እአአ መጋቢት 11/2025
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ፣ የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪ ሲቢሃ፣ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንድሬ የርማክ; ጄዳ፣ እአአ መጋቢት 11/2025

የዩናይትድ ስቴትስ እና የዩክሬን ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ሳዑዲ አረቢያ ላይ በኪየቭ እና ሞስኮ መካከል የከፊል ተኩስ የማቆም ስምነት የታለመ እቅዳቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠበቅበት ንግግር ጀምረዋል።

የዩክሬን እቅድ የረጅም ርቀት የሚሳዬል ጥቃቶችን ማቆም እና ጥቁር ባህርን የሚሸፍን የሰላም ስምምነት ያካትታል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በዛሬው ንግግር አልተሳተፉም። በምትካቸው የፕሬዝደንታዊው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንድሬ የርማክ፣ የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪ ሲቢሃ፣ የመከላከያ ሚንስትሩ ረስተም ኡሜሮቭ እና ወታደራዊ አዛዡ ፓቭሎ ፓሊሳ ተወክለዋል።

የርማክ ከስብሰባው አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት “ሰላምን እንዲመጣ ዩክሬን ሁሉንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነች" ብለዋል።.

ሀገራቸው የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጣት ትሻ እንደሆን የተጠየቁት የርማክ "አዎን! ዩክሬን ሩስያ ይህን መሰል የኃይል ጥቃቷን ፈጽሞ እንደማትደግም ማረጋገጥ ትሻለች" ብለዋል።

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 መጀመሪያ ላይ ሩስያ በዩክሬን ላይ ለከፈተችው መጠነ ሰፊ ወረራ አፋጣኝ ማብቂያ ለማበጀት በያዙት ጥረት የዩናይትድ ስቴትስን ልዑካን ቡድን የመሩት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው ማይክ ዋልትዝ ናቸው።

ሩቢዮ ትላንት ሰኞ ሲናገሩ ዩናይትድ ስቴትስ ለጊዜው የተቋረጠው ለዩክሬን ይሰጥ የነበረው ርዳታ ጉዳይም እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላት አመልክተዋል።

ሩቢዮ አክለውም ከዩክሬይን ጋራ በሚደረገው ንግግር ላበረከቱት አስተዋፆ ብሪታንያን እና ፈረንሳይን አወድሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG