በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ተኩስ ማቆም ላይ ያተኮረውንና በአራት ሃገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዛሬ ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል።
ሩቢዮ ከሳዑዲ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ልዑል ፋይሳል ቢን ፋርጃን አል ሳዑድ ጋራ ሪያድ ላይ የተገናኙ ሲሆን፣ ከአልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋራ እንደሚገናኙም ይጠበቃል።
ሩቢዮ በቀጠናው ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ፍልስጤማውያን ወደ ጎረቤት ሃገራት ተወስደው፣ አሜሪካ ጋዛን ተቆጣጥራ ታልማው የሚል ሃሳብ ባቀረቡበትና ሃሳቡን ሳዑዲ አረቢያም ሆነ ሌሎች አረብ ሃገራት እየተቃወሙ ባለበት ወቅት ነው።
ሃሳቡ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋራ ያላትን ግንኙነት እንድታሻሽል ትረምፕ ያላቸው መሻት ላይም እንቅፋት እንዳይሆን ተፈርቷል። ሳዑዲ ከእስራኤል ጋራ ግንኙነቷን የምታሻሽለው ለፍልስጤም የሃገር እውቅና ከተሰጠ ብቻ መሆኑን ስታስታውቅ ቆይታለች፡፡
መድረክ / ፎረም