በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያው ልዑል ሀሪና የአሜሪካዊቷ የቀድሞ ፊልም ተዋናይ ሜገን መርክል ጋብቻ


የብሪታንያው ልዑል ሀሪ የአሜሪካዊቷ የቀድሞ ፊልም ተዋናይ ሜገን መርክል
የብሪታንያው ልዑል ሀሪ የአሜሪካዊቷ የቀድሞ ፊልም ተዋናይ ሜገን መርክል

በብሪታንያው ልዑል ሀሪ በአሜሪካዊቷ የቀድሞ ፊልም ተዋናይ ሜገን መርክል መካከል ነገ የሚፈፀመው ጋብቻ የቀሩት ሰዓቶች ጥቂት ናቸው።

በብሪታንያው ልዑል ሀሪ በአሜሪካዊቷ የቀድሞ ፊልም ተዋናይ ሜገን መርክል መካከል ነገ የሚፈፀመው ጋብቻ የቀሩት ሰዓቶች ጥቂት ናቸው።

ሥነ ሥርዓቱ የሚፈጸመው ከለንደን ወጣ ብሎ በሚገኘው በዊንሰር ከተማ ነው። ሜገን መርክል አባቷ በሠርጓ ላይ የማይገኙት በህመም ምክንያት መሆኑን አረጋግጣለች።

ነዋሪነታቸው ሜክሲኮ የሆነው አባቷ ቶማስ መርክል ከትላንት በስቲያ ረቡዕ የልብ ቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑ ተዘግቧል።

ነገ በታሪካዊቷ በዊንሰር ከተማ በልዑል ሀሪና ሜገን ማርከል መካከል የሚፈፀመውን ንጉሣዊ ጋብቻ ከቅርብ ሆኖ ለመከታተል ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሕዝብ በአካባቢው እንደሚገኝ ተገምቷል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ከሕዝብ የሚከፈላቸው ፖሊሶች ፀጥታውን እንዲቆጣጠሩ ተመድበዋል።

ሥነ ሥርዓቱ ዕኩለ ቀን ላይ የሚጀምረው ልዑል ሀሪ እአአ በ1984 ዓ.ም ክርስትና በተነሱበት በ14ኛው ክፍለ ዘመን በታነፀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል ተብሏል።

በቦታ ጥበት ምክንያት በቤተ ክርስቲያኑ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኙ የተጋበዙት 6መቶ የሚሆኑ ቅርብ የሙሽሮቹ እንግዶች ብቻ ናቸው።

ሌሎች ከ2ሺህ5መቶ በላይ እንግዶች ዋናው ግብዣ በሚካሄድበት የቤተ መንግሥቱ ግቢ ቅጥር ውስጥ ይታደማሉ።

በዊንሰር ከተማ ግራና ቀኝ ላይ ጎዳናዎች ደግሞ ከ1መቲ ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በደንብ ማየት የሚያስችሉ ቦታዎችን ለመያዝ ሰዉ ከአሁኑ ጥድፊያ መያዙ ተነግሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG