በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰፋኒት ሜጋን ሜርክል - የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አዲስ ደም


የእንግሊዝን ንጉሣዊ ቤተሰብ ይዘት እስከወዲያኛው የለወጠው የልዑል ሃሪና የሜጋን ሜርከል ጋብቻ እጅግ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተከናውኗል።

የእንግሊዝን ንጉሣዊ ቤተሰብ ይዘት እስከወዲያኛው የለወጠው የልዑል ሃሪና የሜጋን ሜርከል ጋብቻ እጅግ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተከናውኗል።

ከለንደን ወጣ ብላ በምትገኘው ዊንድሶር ከተማ በተከናወነው ሥነ-ሥርዓት ላይ ሙሽራዪቱን ይዘው እልጃቸው ሃሪ ዘንድ ያደረሱት ልዑል ቻርልስ ናቸው።

ልዑል ቻርልስ የልጃቸውን እጮኛ ወደ ቃልኪዳን መለዋወጫው ሲወስዱ
ልዑል ቻርልስ የልጃቸውን እጮኛ ወደ ቃልኪዳን መለዋወጫው ሲወስዱ

የሜጋን አባት ታመስ ሜርክል በጤና ምክንያት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

ዛሬ የሰሲክስን መስፍን፣ የቀድሞውን የዌልስ ልዑል ሃሪን ስታገባ የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆነችው አሜሪካዊቱ የቀድሞ ተዋናዪት፣ አሁን የሰሲክስ ሰፋኒት ሜጋን ሜርክል የተገኘችው ከአሜሪካዊያኑ ነጭ አባቷ ታመስ ሜርክል እና ጥቁር እናቷ ዶሪያ ሬግለንድ ነው።

የ31 ዓመቷ ልዕልት ሜጋን ሜርክል የተወለደችውና ያደገችው በካሊፎርኒያዪቱ ሎስ አንጀለስ ከተማ ሲሆን /እአአ/ ከ2011 እስከ 2013 ዓ.ም. ለሁለት ዓመታት ያህል የቆየ የቀደመ ትዳር ነበራት።

የሰሲክስ መስፍን ልዑል ሃሪና የሰሲክስ ሰፋኒት ሜጋን ሜርከል
የሰሲክስ መስፍን ልዑል ሃሪና የሰሲክስ ሰፋኒት ሜጋን ሜርከል

በዓለም ዙሪያ እንደትንግርት በታየው በዛሬው ሥነ-ሥርዓትና ድግሥ ላይ ከተጋበዙት ከሙሽሮቹ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ናቸው ከተባሉ ስድስት መቶ ሠርገኞችና 2 ሺህ 500 ታዳሚዎች በተጨማሪ ሙምባይ-ሕንድ ውስጥ ከወር አበባ ጋር በተያያዙ ማኅበራዊ እንዲሁም የግልና የቤተሰብ አቅም ችግሮች ላይ የሚሠራ ግብረሰናይ ድርጅትም ተጋብዟል።

ሰፊ ዘገባ /በእንግሊዝኛ/ ለማግኘት፤ ለተጨማሪ ፎቶግራፎችና ቪድዮ ከታች የተያያዘውን ማገናኛ ይጫኑ፤ ወደ www.voanews.com ዘገባ ይወስድዎታል። https://www.voanews.com/a/prince-harry-meghan-markle-wed/4401036.html

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG