ሚያንማር ውስጥ(የቀድሞዋ በርማ) ያለውን አመፅ በመሸሽ የተሰደዱ የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ቁጥር የመገናኛ ብዙሃን አጋኖታል ሲሉ፣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ። “አመፁ ከዘር ማፅዳት ጋር የተያያዘ ነው” የተባለውን ዘገባም በብርቱ ተቃውመዋል።
ጀነራል ሚኒ ኦን ሃላይንግ ከዩናይትድ ስቴትሱ አምባሳደር ስኮት ማርሴል ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ ግጭቱ እንዳይበርድ መገናኛ ብዙኃኑ ነዳጅ በመጨመር አባብሶታል ሲሉ በትዊተር እንዳሰራጩ ተናግረዋል።
ወደ ባንግላዴሽ የተሰደዱት የሮሒንግያ ሙስሊሞች ቁጥር ከፍተኛ ነው ብሎ መዘገብ፣ ነገርን ማጋነን ነው ያሉት ጀነራልጦር ኃይሉ አደረሰ የተባለውንም ከልክ ያለፈ ጥቃት አጣጥለዋል።
በተመድ ዘገባ መሠረት፣ ራከሄኒ ግዛት ውስጥ ባለው አመፁ ምክንያት፣ ከ500,000 በላይየሮሒንግያ ፍልሰተኞች ናቸው እአአ ከነሐሴ 25 ቀን ጀምሮ፣ ወደ ጎረቤት ባንግላዴሽ የተሰደዱት።
የተመድ ዛሬ ሐሙስ ይፋ እንዳደረገው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጀፈሪ ፌልትማን ከነገ ዐርብ ጀምሮ እስከ መጪው ማክሰኞ ድረስ ማያንማርን ይጎበኛሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ