በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግድያ ሸሽተው የተሰደዱ የሮሒንግያ ሙስሊምች እንደሚባረሩ በመስማታቸው ፍርሃታቸውን ገለፁ

ባለፈው ዓመት ሚያንማር(በርማ) ውስጥ በወታደራዊው ገዢ መደብ የደረሰውን ግድያ ሽሽት ከሀገር የተሰደዱ ሮሒንግያ ሙስሊሞች፣ ገና ከ2ሺህ 2መቶ በላይ ሰዎች በዚህ ወር ካገሪቱ እንደሚባረሩ በመስማታቸው፣ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ።

ባለፈው ዓመት ሚያንማር(በርማ) ውስጥ በወታደራዊው ገዢ መደብ የደረሰውን ግድያ ሽሽት ከሀገር የተሰደዱ ሮሒንግያ ሙስሊሞች፣ ገና ከ2ሺህ 2መቶ በላይ ሰዎች በዚህ ወር ካገሪቱ እንደሚባረሩ በመስማታቸው፣ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ።

አንዳንዶቹ እንዲያውም፣ «ወደ ራከሂኒ ከመመለስ፣ ራሳችንን በራሳችን ብናጠፋ ይሻለናል» ማለታቸው ተሰምቷል። በራከሂኒ የሚያንማር ወታደራዊ ገዢ መደብ፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማወጁ ይወነጀላል።

“ያለንን ሁሉ አጥተናል፣ አሁን ብንመለስ የሚጠብቀን ግድያና ወከባ ነው” ሲል ማንነቱ እንዳይታወቀ የፈለገ ስደተኛ በሰጠው ቃል፣ “ይገደላሉ” ተብሎ ስም ዝርዝራቸው ከተሰጠው መካከል እንደሆነም ተናግሯል።

በዚህ በኅዳር ወር አጋማሽ፣ የሮሒንግያ ስደተኞችን ለመመለስ፣ ሚያንማር እና ባንግላዴሽ ሥምምነት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG