ዋሺንግተን ዲሲ —
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ ፖለቲካ አማካሪ ሮጀር ስቶን - ዛሬ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፣ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል።
ሮጀር ስቶን የቀድሞው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር በነበሩት በሮበርት ሙለር በሚመራውና - የሩሲያን በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብነት በሚያጣራው ልዩ ምክር ቤት ሰባት ክሶች ይጠብቋቸዋል።
የሃሰት መግለጫና ማብራሪያ መስጠት፣ በምርጫው በተደረገ ጣልቃ ገብነት ለተፈጸመ ጉቦ እማኝ በመሆን እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተያዘውን ቃለ ጉባዔና መረጃ ማጥፋት - የቀድሞው የትረምፕ ፖለቲካ አማካሪ ከሚከሰሱባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።
ሞስኮ በ2016 ከተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጣልቃ ገብታለች ስትል ዋሺንግተን ትከሳለች። ለዚህም በርካታ ሩሲያውያን ላይ ምርምራ እያደረገች ሲሆን፥ ሮበርት ሙለርም ይህን ለማጣራት የተቋቋመውን ልዩ ምክር ቤት ይመራሉ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ - የሚናፈሰው ወሬ አሉባልታ ነው በሚል ውንጀላውን ውድቅ ያደርጋሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ