በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካርቱም በፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ ድሮኖች ስትደበደብ ዋለች


ፎቶ ፋይል፦ ካርቱም፤ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፦ ካርቱም፤ ሱዳን

የሱዳን ዋና መዲና ካርቱም፣ በዛሬው ዕለት በሮኬትና በድሮን ስትደበደብ ዋለች። ፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ፣ በመዲናዪቱ ሰሜን አቅጣጫ የሚገኝን ቁልፍ የአየር ኃይል ማረፊያ ማጥቃቱንና በደርዘን የሚቆጠሩ የሠራዊት አባላትን መግደሉን አስታውቋል።

በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ፣ የከባድ መሣሪያ ድብደባ እንደነበርና የፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ ድሮኖች፣ በሰሜን ካርቱም የሚገኝ የአየር ኃይል ማረፊያን ማጥቃታቸውን፣ ኤኤፍፒ የነዋሪዎችን ቃል ጠቅሶ ዘግቧል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ፥ ሦስት ተዋጊ ጄቶችን፣ በርካታ መሣሪያዎችን፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችንና አቅርቦቶችን ማውደሙን አስታውቋል። በደርዘን የሚቆጠሩ የአገሪቱ ሠራዊት አባላትንም መግደሉን ወይም ማቁሰሉን አክሎ ገልጿል።

በካርቱም እና በምዕራብ ዳርፉር፣ ከሚያዝያ 15 ቀን ጀምሮ እየተካሔደ ባለው ውጊያ፣ 3ሺሕ 900 ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ3ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG