በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካቡል የዲፕሎማሲ ተቋማት በሮኬቶች መመታቱ ተዘገበ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል የዲፕሎማሲ ተቋማት በሚገኙበት ቀበሌ በዛሬው ዕለት በበርካታ ሮኬቶች መመታቱ ተዘገበ።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል የዲፕሎማሲ ተቋማት በሚገኙበት ቀበሌ በዛሬው ዕለት በበርካታ ሮኬቶች መመታቱ ተዘገበ። ይህ የሆነው የሃገሪቱ ፕሬዚደንት አሽራፍ ጋኒ የዛሬውን የኢድ በዓል ምክንያት በማድረግ መልዕክታቸውን በማሰማት ላይ እንዳሉ መሆኑ ታውቁዋል።

የሃገሪቱ ፖሊሶች እንደተናገሩት ሮኬቶቹ የተተኮሱ ከከተማዋ ውጭ ካለ ስፍራ ሲሆን አንዳንዶቹ ቤተ መንግስቱና ኤምባሲዎች አቅራቢያ ወድቀዋል።

ፕሬዚደንት ጋኒ በኢድ በዓል መልዕክታቸው ጥቃቶቹን አውግዘዋል። ፕሬዚደንቱ ከታሊባን ጋር ተመሳሳይ ርምጃ የሚወስድ ከሆነ እስከሶስት ወር የሚፀና ተኩስ አቁም እናደርጋለን ሲሉ ባለፈው ዕሁድ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG