በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በከተማዋ ጨምሯል የተባለው የግንባታ ላይ አደጋ


በከተማዋ ጨምሯል የተባለው የግንባታ ላይ አደጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:37 0:00

በከተማዋ ጨምሯል የተባለው የግንባታ ላይ አደጋ

በአዲስ አበባ፣ በዘጠኝ ወራት ብቻ፣ 13 ሰዎች በግንባታ ወቅት በተከሠተ አደጋ መሞታቸውን፣ የከተማዋ እሳት እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ይህ አኃዝ ተቋማቸው ለርዳታ ተጠርቶ በሔደባቸው የተመዘገበ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ መሰል አደጋም በከተማዋ እየጨመረ መምጣቱን ያመለክታሉ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው ስትራክቸራል መሐንዲስ እና የሥራ ላይ ደኅንነት ባለሞያዋ ቤዛ በቀለ፣ የግንባታ ተቋራጮች የሥራ ላይ ደኅንነት መከላከያን እንደ ተጨማሪ ወጭ የማየትና ትኩረት ያለመስጠት ችግር፣ ለአደጋው መባባስ ምክንያት መኾኑን ያስረዳሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG