በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ሊቢያ የታሠሩት ሙዚቀኛና ጦማሪ እንዲለቀቁ ጥሪ ቀረበ


የመረጃ ሕጉን ተላልፈዋል በሚል ምሥራቅ ሊቢያ ውስጥ ታስረው የሚገኙትን አንድ የሙዚቃ አቀንቃኝና አንድ ጦማሪ ከእስር እንዲለቀቁ ፤ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ወች ጥሪ አቀረበ፡፡

በአገሪቱ ታዋቂ አቀንቃኝ የኾነችው አህላም አል ያማኒ እና ጦማሪዋ ሃኒን አል አብዳሊ ከሥነ-ምግባርና ከኃይማኖት ያፈነገጠ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ባለፈው ወር በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

በምሥራቃዊቷ ቤንጋዚ ከተማ የሚገኘው የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ “ወግ አጥባቂ በኾነው ማኅበረሰብ ባዕድ የሆኑ ባሕልና ኃይማኖትን የሚጻረሩ እንዲሁም ሴቶች መፈጸም ያማይገባቸውን ድርጊት ፈጽመዋል” ብሏል፡፡ መግለጫው አያይዞም “ባለፈው መስከረም የወጣውን የመረጃ መረብ ሕግ ተላልፈዋል” ብሏል።

የሁለቱን ሰዎች እስር ተቃውሞ መግለጫ ያወጣው ሂዩማን ራይትስ ወች፤ “የመረጃ መረብ ሕጉ ቀድሞውንም መሠረታዊ መብቶችን የሚጥሱ ሕጎች በወጡበት አገር ላይ ተጨማሪ እገዳን የሚጥል ነው” ብሏል። “ግልጽ ያልሆነና የተለጠጠ” ያለውን የወንጀል ሕግ ፓርላማው እንዲሽረውም ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG