በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ባለታሪክ ፖል ሩሲሳቢጊና የእስር ቅጣት ተወገዘ


"ሆቴል ሩዋንዳ” የተሰኘው ዝነኛ ፊልም ታሪካቸው የተወሳላቸው ሩዋንዳዊ ፖል ሩሲሳቢጊና
"ሆቴል ሩዋንዳ” የተሰኘው ዝነኛ ፊልም ታሪካቸው የተወሳላቸው ሩዋንዳዊ ፖል ሩሲሳቢጊና

"ሆቴል ሩዋንዳ” የተሰኘው ዝነኛ ፊልም ታሪካቸው የተወሳላቸው ሩዋንዳዊ ፖል ሩሲሳቢጊና ላይ የሩዋንዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የ25 ዓመት የእስራት ቅጣት መወሰኑን ራይት ግሩፕ የተሰኘው ለሰብዓዊ መበት መብት ተከራካሪ ድርጅት አወገዘ፡፡

ፍ/ቤቱ ሰኞ ዕለት እሳቸውን እና አብረዋቸው በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጥፋተኛ ያላቸው፡ ሩሲሳባጊና ክሱን አስተባብለዋል፡፡ ተቺዎችም መታሰራቸውም ሆነ የክስ ሄደቱ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ሥርዓቱን ያከበረ አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

በሩዋንዳ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ወደ ኬኒያ የተሰደዱት ባሂማ ማኩማ የሩሲሳባጊናን የፍርድ ሂደት በቅርብ የሚከታተሉ ሲሆኑ፡ የሩዋንዳ መንግሥት ማንንም መስማት አይፈልግም፡፡ የመስማቱን እድል ሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ግን እኚህ ሰው ከ1000 በላይ ሰዎችን ከግድያ ያተረፉ መሆናቸው ይታወቅ ነበር፡፡

“ከ1000 ሰዎች በላይ ህይወት የታደገ ሰው ሽብርተኛ ከተባለ አንድም ሰው ያላተረፈው ምን ሊባል ነው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ዓለም በሙሉ ሩሲሳባጊና በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት አደጋ ውስጥ የነበሩ የቱትሲ እና ሁቱዎችን በኪጋሊ ሆቴል ውስጥ እራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የደበቁ ጀግና የሚመለከታቸው ሲሆን የሩዋንዳ መንግሥት ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜን ለመጣል ከተነሱ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በመተባበር ይከሳቸዋል፥ በሚሰነዝሩት የሰላ ሂስ በአደገኛነት ይመለከታቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG