በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄሲ ጃክሰን በኅዳሴና በአባይ ጉዳይ ደብዳቤ ላኩ


ጄሲ ጃክሰን - /ፎቶ ፋይል/
ጄሲ ጃክሰን - /ፎቶ ፋይል/

የአባይን ውኃና ኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ ግብፅ በላከችለት ደብዳቤ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አንዳች እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ጥቁር እንደራሴዎች ክንፍ ፈጥኖ ጠንካራ መግለጫ እንዲያወጣ “ቀስተዳመና / ሰብዕናን ለመታደግ የተባበረ ሕዝብ” የሚባለው አሜሪካዊ ጥምረት መሥራችና መሪ ቄስ ጄሲ ጃክሰን ጠየቁ።

ከወጣትነት ዕድሜአቸው አንስቶ ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር የሲቪል መብቶች ተሟጋችና ተደማጭም የሆኑት ጄሲ ጃክሰን በድርጅታቸው ስም በፈረሙበትና ለጥቁር እንደራሴዎቹ ኅብረት ሊቀመንበር ካረን ባስ ከትናንት በስተያ በላኩት ደብዳቤ ላይ የኅብረቱ መግለጫ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም. ከወጣው የቅኝ ግዛት ውል የተቀዳውን ግብፅ “በናይል ላይ ያሉኝ የውኃ መብቶቼ” የምትለውን አቋሟን የሚደግፈውን የአረብ ሊግ ውሣኔ የሚቃወም እንዲሆን ጠይቀዋል።

በቄስ ጄሲ ጃክሰን ደብዳቤ ላይ የተሰናዳውን አጭር ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጄሲ ጃክሰን በኅዳሴና በአባይ ጉዳይ ደብዳቤ ላኩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:23 0:00

የቄስ ጄሲ ጃክሰን ሙሉ ደብዳቤ ከዚህ ዘገባ ጋር ተያይዟል።

FILE - ቄስ ጄሲ ጃክሰን July 27, 2016.
በአባይ ውኃና በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ቄስ ጄሲ ጃክሰን ለዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ጥቁር እንደራሴዎች ኅብረት ሊቀመንበር ካረን ባስ የላኩት ደብዳቤ

XS
SM
MD
LG