በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የጭነት መኪና ሾፌሮች አድማ ለመምታት አቅደዋል


የኮቪድ-19 ግዴታዎችን ለመቃወም የተሰናዳ የጭነት መኪና አዴላንቶ፣ ካሊፎርኒያ እአአ ፌብሩዋሪ 22/2022
የኮቪድ-19 ግዴታዎችን ለመቃወም የተሰናዳ የጭነት መኪና አዴላንቶ፣ ካሊፎርኒያ እአአ ፌብሩዋሪ 22/2022

የካናዳ ዋና ከተማን ለሳምንታት ያሽመደመደውን መሳይ አድማ በዩናይትድ ስቴትስ ለማድረግ የጭነት መኪና ሾፌሮች ማቀዳቸው ተሰምቷል።

ሾፌሮቹ፣ የኮሮናቫይረስ የእግድ ደንቦችን በመቃወም መዳረሻውን በመዲናዋ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ የ4000 ኬሎ ሜትሮች ጉዞ ለመድረግ ወስነዋል።

ሮይተርስ ‘People's Convoy’ የተሰኘውን አስተባባሪ ቡድን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሾፌሮቹ ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ሀገሪቱን ዳግም ክፍት የማድረግ ግብ አላቸው ብሏል።

11 ቀናትን የሚፈጀው የሾፌሮቹ የተቃውሞ ጉዞ፣ ወደ ዋና ከተማዋ ዘልቆ ሳይገባ በአቅራቢያው ባለ የቀለበት መንገድ ላይ በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 ለመገኘት እንዳለመ የአስተባባሪው ቡድን መግለጫ ያመለከታል።

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ መሥሪያ ቤት በተዘጋጁ የትራፊክ ቀጠናዎች ድጋፍ የሚሰጡ፣ አስፈላጊ ትዕዛዞችን የሚሰጡ የሚቆጣጠሩ እና አስፈላጊ ጉዳዮችን የሚከውኑ 400 የብሄራዊ ዘብ አባላትን መድቧል። ከዚህ በተጨማሪም 50 የጦር መኪኖች በጎዳናዎች ላይ ዝግጁ ሆነው እንዲቆሙ ፍቃድ ተሰጥቷል።

ብሪያን ብራስ የተባሉ ሾፌር እና አስተባባሪ መኪኖቹ የትም ይቁሙ የት፣ “ጥያቄያችን ካልተመለሰ የትም አንሄድም!’’ ብለዋል። ከጥያቄዎቻቸው መካከል የኮቪድ ክትባት እና የፊት ጭንብል አስገዳጅነት እንዲቀር የሚጠይቀው ይገኝበታል።

XS
SM
MD
LG