በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመራማሪዎችን እያሳሰበ ያለው ዴልታ ፕለስ


እስራኤል ውስጥ አንድ የአስራ አንድ ዓመት ልጅ ላይ በፍጥነት ተላላፊ የሆነው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የዴልታ ዘር ሆኖ ዘረ መሉን የቀየረ ቫይረስ እንደተገኘ ተገለፀ።

“ኤዋይፎርቱ” የሚል ስያሜ የወጣለት አዲስ የዴልታው ልውጥ ዝርያ አይነት በዓለም ዙሪያ ተመራማሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል።

የእስራኤል የጤና ባለሥልጣናት ከሞልዶቫ ወደቴልአቪቭ በቤን ጊዩሪዮን አውሮፕላን ጣቢያ በኩል በገባው ልጅ ላይ አዲሱ የዴልታ ልውጥ ዝርያ ቫይረስ እንደተገኘ በዚሁ ሳምንት ውስጥ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ልጁ ወዲያውኑ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ መደረጉን እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ተጠቁሟል።

ዴልታ ፕለስ የሚባለው አዲሱ የዲልታ ቫይረስ ዝርያ እንግሊዝ ሩስያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥም ተገኝቷል።

ሳይንቲስቶች ይህ ራሱን ቀየር አድርጎ ብቅ ያለ ዴልታ በዓለም ዙሪያ ባለፉት ጥቂት ወራት ለብዙ ሰዎች መጋለጥ ምክንያት ከሆነው ከቀደመው የዴልታው ዓይነት በይበልጥ የሚተላለፍ ይሆን እንደሆን እንዲሆም በክትባት ያለመበገር ባህሪ ይኖረው እንደሆን ለጊዜው ድምዳሜ ላይ አልደረሱም። የዓለም የጤና ድርጅትም "ትኩረት የሚያስፈልገው" ወይም "አሳሳቢ" ብሎ አልፈረጀውም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህንድ ለባለዝቅተኛ ገቢ ሀገሮች የኮቪድ ክትባት ለማዳረስ ለሚሰራው ለኮቫክስ ማቀረብ የነበረባትን ክትባት እንዳዘገየች ሮይተርስ ዘገበ።

በሌላ ዜና የኮቪድ ክትባት ዜና ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ እንደዘገበው ለዐለም እጅግ ድሃ ሃገሮች ለመለገስ ቃል ከተገባው የኮቪድ ክትባት ውስጥ እስካሁን የደረሰው ከሰባት ክትባት አንድ ብቻ እንደሆነ አንድ አዲስ ሪፖርት ጠቆመ።

ኦክስፋም እና አምነስቲ ኢንተርናሲናልን ያካተተ የህዝብ የኮቪድ ክትባት ጥምረት እንዳለው ባለጸጎቹ ሃገሮች አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ነጠላ ክትባቶችን ለመለገስ ቃል ገብተዋል፣ ነገር ግን እስካሁን የላኩት 261 ሚሊዮን ወይም አስራ አራት ከመቶውን ብቻ ነው።

XS
SM
MD
LG