በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወባ በሽታ በአፍሪካ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አፍሪካ ውስጥ በመድሃኒት የማይበገር የወባ በሽታ ዓይነት መኖሩን ሳይንቲስቶች ዩጋንዳ ውስጥ ማስረጃ እንዳገኙ ተገለፀ። መድሃኒት የማይገታው የወባ ዐይነት እንዳይስፋፋ መላ ካልተፈለገ በስተቀር በዋናነት ለህክምና የሚውለውን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል የሚል ሥጋት ቀስቅሷል።

እአአ በ2019 ዩጋንዳ ውስጥ ለጥናቱ ምርመራ ከተደረግባቸው የህሙማን የደም ናሙናዎች ውስጥ ሃያ ከመቶው ላይ የዘረ መል ለውጥ መታየቱ ነው የተገለፀው።

ካሁን ቀደም እስያ ውስጥ ተመሳሳይ የወባ ዘረ መል ለውጥ የታየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው ሆኖም በዓለም ላይ ካሉት የወባ ህሙማን ውስጥ ዘጠና ከመቶው ያሉት አፍሪካ ውስጥ መሆኑን ጥቁሟል።

XS
SM
MD
LG