በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብራዚል የነፍስ አድን ሠራተኞች ተመሳሳይ አደጋዎች ባንዣበቡት ሁኔታ ነፍስ ለማዳን እየጣሩ ነው


በሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል በጣለው ከባድ ዝናብ ሰዎች ጎዳናው ላይ ይራመዳሉ፤ ብራዚል እአአ ግንቦት 9/2024
በሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል በጣለው ከባድ ዝናብ ሰዎች ጎዳናው ላይ ይራመዳሉ፤ ብራዚል እአአ ግንቦት 9/2024

የደቡባዊ ብራዚል ባለስልጣናት ቢያንስ 100 ሰዎችን ከገደለው ግዙፍ የጎርፍ አደጋ የተረፉትን ሰዎች ለመታደግ ትላንት ሐሙስ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡

አንዳንድ ነዋሪዎች ግን አካባቢያቸውን ለቀው ለመሄድ ፈቃደኛ አልሆኑም ሲል አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

አንዳንዶቹ ንብረታቸውን ትተው መሄድ አልፈለጉም፡፡ ሌሎች ደግሞ ከባድ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ እንደሚፈጠር ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ወደ የቤቶቻቸው ተመልሰዋል።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሪዮ ግራንዴ ዶ ሱል በጣለው ከባድ ዝናብ እና የጎርፍ አደጋ፣ 130 ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

በአደጋው ከ230,000 በላይ የሚሆኑት ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ የክልሉ አብዛኛው ክፍል አካባቢውን ባጥለቀለቀው የጎርፍ ውሃ ተነጥሏል፡፡

የብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ተቋም በነገው ቅዳሜና እሁድ ቅዝቃዜ እንደሚከሰት ሲተነብይ፣ በተለይ በግዛቱ ሰሜን እና ምስራቅ አካባቢዎች የሚጥለው ዝናብ ከባድ ይሆናል ብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG