በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቨርጂኒያ ሪፐብሊካኑ ግሊን ያንግኪን አሸነፉ


ሪፐብሊካኑ ግሊን ያንግኪን
ሪፐብሊካኑ ግሊን ያንግኪን

ትናንት ለቨርጂኒ በተደረገ ምርጫ ሪፐብሊካኑ ግሊን ያንግኪን ዴሞክራቱን ተቀናቃኛቸው ቴሪ መካለፍን 51 ለ48 ከመቶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሚቀጥለው የቨርጂኒያ ገዥ ለመሆን ተዘጋጅተዋል፡፡

በዴሞክራቲክ ክፍለ ግዛት በምትታወቀው በኒው ጀርሲም ተመሳሳይ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ተጠናቆ አልተገለጸም፡፡ ይሁን እንጂ ዴሞክራቱ ፊል መርፊ ከተቀናቃኛቸው ጃክ ሲያታረሊ ትንሽ በለጥ ብለው ቢታዩም እጅግ በተቀራረበ ርቀት እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡

በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ትናንት በተካሄዱ ምርጫዎች ውጤቶች እየተገለጹ ሲሆን ለኒው ዮርክ ከንቲባነት በተደረገው ውድድር ዴሞክራቱ ኤርክ አደምስ ማሸነፋቸው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG