በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሪፓብሊካን ፓርቲ ፕረዚደንት እጩ ተወዳዳሪዎች ክርክር


ለአሜሪካ ፕረዚደንትነት የሚወዳደሩ የሪፓብሊካን ፓርቲ እጩዎች በአይስስ (ISIS) ለማጥፋት ሚቻልበት ፖሊሲ ላይ ተከራከሩ።

ትላንት በዩናትድ ስቴትስ (United States) ለፕረዚደንትነት የሚወዳደሩት ሪፓብሊካን ባካሄዱት አምስተኛ ዙር ክርክር አብይ ቦታ የያዙት ነጥቦች ብሄራዊ ጸጥታና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት በሚታዩት የአሸባሪዎች ጥቃቶች ምክንያት አሜሪካውያንን የሚያሳሰበው የጸጥታ ደህንነት ጉዳይ እንደሆነ የህዝብ አስተያየት መለኪያ አሃዞች አመላክተዋል።

ለፕረዚዳንትነት ከሚወዳደሩት ሪፑብሊካውያን ቀዳሚ ቦታ የያዙት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካውያን ያልሆኑ ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ አግዳለሁ በማለታቸው በክርክሩ ወቅት ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። የቀድሞ የፍሎሪዳ ክፍለ-ግዛት አስተዳዳሪ ጄብ ቡሽ በጉዳይ ላይ አጥብቀው ተከራክረዋቸዋል።

ሪፓብሊካዊው ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ “ስለ ሀይማኖታዊ እምነት አይደልም የምንናገር ያለነው ስለ-ጸጥታ ጉዳይ ነው። ሀገራችን ከቁጥጥር ውጭ ሆናለች” ብለዋል።

የሪፓብልካዊው ተውዳዳሪ ጄብ ቡሽ ምላሽ፣ “እንዲህ አይነቱ አመለካከት የሙስሊሙ አለም ከኛ እንዲርቅ ያደርጋል። ይልቁንስ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድን ለማጥፋት ስትራቴጂ በማውጣት ረገድ ከሙስሊሙ አለም ጋር መስራት ይኖርብናል። ዶናልድ ለፌዝ አንጋገር ያመቻል። ሆኖም የረብሻ ተወዳዳሪ ነው። የትርምስ ፕረዚዳንትም ነው ሊሆን የሚችለው” በማለት መልሰውላቸዋል።

ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ለፕረዚዳንትነት ቢመረጡ ሩስያን በሚመለከት ጠንካራ አቋም የሚይዘው የትኛው ነው? በሚል ነጥብም ላይ ተጋጭተዋል።

የተወዳዳሪዎቹ ክርክር በአብዛኛው ያተኮረው እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድንን ለማሸነፍ ስለሚቻልበት ጉዳይ ነው። በተለይም ሪፑብሊካዊው የቴክሳሱ ሴኔተር ቴድ ክሩዝና ሪፑብሊካዊው የፍሎሪዳው ሴኔተር ማርኮ ሩብዮ ቅድሚያ የሚሰጡበት ጉድይ ነው።

ቴድ ክሩዝ“ከፍተኛ የአየር ሃይል መጠቀም አለብን። ኩርዶችን ማስታጠቅ ይገባናል። እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚውልን ቡድን መታገልና በያለበት መገደል ያስፈልገናል”ብለዋል።

ሩብዮ “አይስስ (ISIS) ጽንፈኛ የሱኒ ሙስሉም ቡድን ነው። በአየር ድብደባ ብቻ ሊሸነፍ አይችልም። የአየር ድብደባው ወሳኝ ቢሆንም በየብስም በወታደራዊ ሀይል መሸነፍ ይኖርበታል” ብለዋል።

የኦሃዮ ክፍለ-ግዛት አስተዳዳሪ ጆን ካሲች (John Kasich) ደግሞ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድን ለማሸንፍ ውህደት መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።“ከሁሉ አስቀድመን ሄደን ISISን ማጥፋት አለብን። ይህን ማደረግ ያለብንም ከወዳጆቻችን የአረብና የአውሮፓ ሀገሮች ጋር በመተባበር ነው።”

የኬንታኪ ክፍለ-ግዛት ሴኔተር ራንድ ፖል ግን ያለፈው ስህተት እንዳይደገም አስጠንቅቀዋል። “የሶርያውን ፕረዚዳንት ባሽር ዐል-ዐሳድን ከስልጣን ለማስወገድ የሚፈልጉት ሰዎች ብዙ ናቸው። ያቢሆን ትርምስ ይፈጠርና ISIS ስልጣን የሚይዝ ይመስለኛል።”

ሪፑብሊካውያኑ ተወዳዳሪዎች አሜሪካን ከአሸባሪዎች ጥቃት ለመጠበቅ በሚቻልበት መንገድም መጋጨታቸው አልቀረም።

የኒው ጀርሲ ክፍለ-ሀገር አስተዳዳሪ ክሪስ ክሪስቲ ህግ አስከባሪዎች ሁኔታዎችን በሚገባ የመከታተልና የመሰለል ብቃት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል በማለት ተከራክረዋል።

“ልንገራችሁና እኔ በፌደራል አቃቤ-ህግነት ሰራቻለሁ። አሸባሪዎችን ታግየ አሸንፌያለሁ። በዋይት ሃውስ ስንገባም አሸባሪዎችን ታግለን ደግመን እናሸንፋለና የአሜሪካ ደህንነት ይጠበቃል።”

የሪፑብሊካውይኑ ተወዳዳሪዎች ቀጣዩ ዙር ክርክር በመጪው ጥር ወር ይካሄዳል።የአሜሪክ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ጂም መሎነ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች።

የሪፓብሊካን ፓርቲ ፕረዚደንት እጩ ተወዳዳሪዎች ክርክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG