በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናዩትድ ስቴትስ በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ ጥፋትና ውድመቶች አሳስቦኛል አለች


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

ዩናዩትድ ስቴትስ በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ ጥፋትና ውድመቶች አሳስቦኛል አለች።

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ኃይሎች በአማራና አፋር ክልሎች ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችና የመሰረት ልማት ውድመቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ሲል መግለጫ አወጣ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት በሰጡት መግለጫ “ሁሉም ታጣቂ ወገኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዲያቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

“ባለሥልጣናቱም እነዚህን መረጃዎች በመመርመር ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለይቶ ለማውጣት ግልጽና ሁሉን አሳታፊ የሆነ የምርመራ ሂደት እንዲጀምሩ እናሳስባለን” ማለታቸውም ተመልክቷል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው፣ “ዩናይትድ ስቴትስ ልክ የሰብዓዊ መብት ጥቃትና ጥሰቱ እንዲያበቃ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንዲደረግ፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖርና ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ንግግር እንዲጀመር፣ እንዳሳሰበችው ሁሉ፣ ግጭቱን ለማቆምም የምትሰጠው ድጋፍ የመጀመሪው የመጨረሻውና ብቸኛው አማራጭ ዲፕሎማሲ ብቻ መሆኑን በማመን እንደሆነ በድጋሚ ታረጋግጣለች” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG