በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ፖሊሶች ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ሲፒጄ ከሰሰ


የሲፒጄ አርማ
የሲፒጄ አርማ

በትግራይ የተቃውሞ ሰልፍ ሊዘግቡ የወጡ ሶስት ጋዜጠኞችን ፖሊሶች ደብድበው አስረዋል ሲል የጋዜጠኞች ተሟጋች ቡድኑ ሲፒጄ ከሰሰ።

ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ 2፣ 2015 በክልሉ መዲና መቀሌ በክልሉ አስተዳደር ተከልክሎ የነበረውን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍን ጋዜጠኞቹ ሲቀርጹ በነበረበት ወቅት መሆኑን ሲፒጄ አስታውሷል።

መለዮ የለበሱ ፖሊሶች አስቁመው በዱላ እና በኮረንቲ ገመድ እንደመቷቸው፣ የያበለ ሚዲያ ሪፖርተር ተሻገር ጽጋብ እና የአያም ሚዲያ ተባባሪ መሥራቾች መሃሪ ካህሳይ እና መሃሪ ሰለሞን ለሲፒጄ ተናግረዋል።

“በጋዜጠኞቹ ላይ የደረሰው ድብደባ በትግራይ ያሉ ባለስልጣናት ሪፖርተሮች መንግስትን የሚተቹ ጉዳዮችን እንዲዘግቡ እንደማይፈልጉ አሳዛኝ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ብሏል ሲፒጄ በመግለጫው።

“የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ክስተቱን መርምሮ ፖሊሶቹን ተጠያቂ እናዲያደርግ እንዲሁም ጋዜጠኞች የተቃውሞ ሰልፎችን እና የተቃውሞ ድምጾችን መዘገብ መቻላቸውን እንዲያረጋግጥና የበቀል ጥቃት እንዳይውስድ” ሲል የመብት ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል።

መሃሪ ካህሳይ ከሁለት ቀናት በኋላ ሲልቀቅ፣ መሃሪ ሰለሞን ደግሞ ከአራት ቀናት በኋላ መለቀቃቸው ታውቋል።

በመቀሌ የተጠራው ሰልፍ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ ቅሬታ ያላቸው እና አስተዳደሩ “የፈላጭ ቆራጭነት ጸባይ” ያሳያል ባሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ነበር።

በቂ የፖሊስ ኃይል የለም በሚል አስተዳደሩ ሰልፉን ከልክሎ ነበር።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደት የአቶ ጌታቸው ረዳን መልስ ለማካተት ሞክሮ መልስ እናዳላገኘ ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG