በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምናይ የምንሰማው ሁሉ የግድ ዕውነት ነው ማለት አይደለም!


ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ እና አዲሱ ፍሬው
ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ እና አዲሱ ፍሬው

ያን የሰነበተ ነገር ግን ብርቱ ጥያቄ ለመጠየቅ ጊዜው የሚያስገደድ ይመስላል።

ለመሆኑ እውነት ምንድር ነች?

ከተጨባጩ ዓለም ስሙም የሆነ ሁኔታ ወይም ድርጊት? .. እርስ በእርሱ የማይጣረስ፡ ያልተዛባ ወይም ተፈትሾ በማረጋገጫ ሊረጋገጥ የሚችል መደምደሚያ? .. ወይንስ በተቃራኒ ከቆመው ሃሰት ወይም ውሸት ጋር ተነጻጽሮ የሚመዘን ጭብጥ?

በማሕበራዊ ሚዲያው አውድ የሚታዩና የሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው የተዛቡ ኢትዮጵያ ነክ መረጃዎች ከበረታ አደጋ ላይ የወደቀውን የማሕበረሰቦችን አብሮ የመኖር እሴት ይበልጥ ወደ ተባባሰ አቅጣጫ እየገፉት ይመስላል።

ተወያዮች፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና የኮምዩኒኬሽንስ ትምሕርት ቤት መምሕሩ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው፤ የዩናይትድ ስቴትሱ የኬንት ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽንስ ትምሕርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ እና የኢንተርኒውስ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ማበልጸጊያ ድርጅት “ኢትዮጵያ ቼክ” የተባለው የመረጃ ማጣሪያ ፕሮግራም የመረጃ አጣሪ ባለሞያው አዲሱ ፍሬው ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ክፍል አንድ:- የምናይ የምንሰማው ሁሉ የግድ ዕውነት ነው ማለት አይደለም!
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:09 0:00

ክፍል ሁለት:- የምናይ የምንሰማው ሁሉ የግድ ዕውነት ነው ማለት አይደለም!
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:58 0:00


XS
SM
MD
LG