በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንደራሴ ኬረን ባስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ


የካሊፎርኒያዋ እንደራሴ ኬረን ባስ
የካሊፎርኒያዋ እንደራሴ ኬረን ባስ

በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት የካሊፎርኒያዋ እንደራሴ ኬረን ባስ ሰሞኑን በኢትዮጵያ በታዋቂው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ በተፈጸመው ግድያና ከግድያው ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ሁከት በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል።

ለኢትዮጵያዊው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰብ ከሱ መገደል ተከትሎ በተፈጠሩ ሁከቶች ሰለባ ለሆኑትም ሰዎች ቤተሰቦች ሃዘኔን እገልፃለሁ ብለዋል።

የካሊፎርኒያዋ ዲሞክራት የየዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ኬረን ባስ በመግለጫቸው አስከትለውም የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፆች ሊሰሙ ይገባል፤ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ የመሰባሰብ መብቱ መከበር አለበት ብለዋል።

በሀገሪቱ አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ ውጥረት የነገሰበት እና ዜጎች ቁጣ ላይ የሚገኙበት ነው ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ አባልዋ መንግሥት ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚሰራ ፍትሃዊ መፍትሄ አቅርቦ መምራት የሚገባበት ወቅት ነው ብለዋል፤

የኢትዮጵያ መንግሥት በያዛቸው የለውጥ ሥራዎቹ እንዲቀጥል እና የኢንተርኔት አገልግሎት መዝጋቱን እንዲያቆም አበረታታለሁ ብለዋል።

አክለውም መንግሥት ለዓመታት በጎሳ ብጥብጥ በዳሸቀው አካባቢ ሰላምና መረጋጋትን እንዲያሰፍን ጥላቻና ሁከት በመቀስቀስ በሀገሪቱ ክፍፍል እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑትን በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርብ የሚያበረታቱ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበሯ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG