በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ባገረሸው የሚሊሻዎች ግጭት አምስት ሰዎች ተገደሉ


ትሪፖሊ፣ ሊቢያ
ትሪፖሊ፣ ሊቢያ

የሊቢያ ባለሥልጣናት “አፈንጋጮቹ” ሲሉ በጠሯቸው በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ ሚሊሻዎች መካከል በተነሳ የርስ በርስ ግጭት የ10 ዓመት ታዳጊ ሴት ልጅን ጨምሮ ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎች 13 ደግሞ መቁሰላቸውን አስታወቁ፡፡

በሚሊሻዎቹ መካከል ባላፈው እሁድ ምዕራብ ሊቢያ ውስጥ በተቀሰቀሰው ግጭት እስከ ዛሬ ሰኞ ድረስ መቀጠሉንም ባለሥልጣኖቹን ጠቅሶ አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የሰሞኑ ግጭት በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ለአስር ዓመታት የዘለቀው ጥቃት የቅርብ ጊዜ ክስተት መሆኑም ተገልጿል፡፡

"ዛውያ" በተባለቸው ምዕራብ ሊቢያ በምትገኘው ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት በነዳጅ ዘይት እንደበለጸጉት ብዙዎቹ ከተሞች ታጣቂዎቹ ቡድኖች የበላይነቱን ለመያዝ በመፎካከር የተፈጠረ መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ባላፈው ነሀሴ በአገሪቱ መዲና ትሪፖሊ በተፈጠረ ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸው ሲነገር በበርካታ ወራት በሊቢያ የደረሰ ትልቁ እልቂት ነው ተብሏል፡፡

እኤአ በ2011 በኔቶ በተደገፈው ህዝባዊ አመጽ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋዳፊ ከሞቱ በኋላ በተፈጠረ ሁከት ሊቢያ በትልቅ ቀውስ ውስጥ መወደቋ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ሊቢያ የተለያዩ አፈንጋጭ ሚሊሻዎች በሚደገፉ የየአካባቢው አስተዳደሮች የተከፋፈለች መሆኗም ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG