በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ችግሯ መፈታቱን አስታወቀች

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በንባብ ያሰሙት የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም። ፎቶ፡ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ስክሪን ቅጂ።
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በንባብ ያሰሙት የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም። ፎቶ፡ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ስክሪን ቅጂ።

የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ችግር በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት መፈታቱን ቤተክርስቲያኒቱ አስታወቀች። ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቱ በወከለቻቸው አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ሰፊ ውይይት ተደርጎ ችግሩ መፈታቱን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ከዚሁ የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ጋራ በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ የእምነቱ አስተማሪዎችና ወጣቶች አዳንዶቹ ቦሌ አካባቢ ያለ መኖሪያ ቤት ውስጥ መታሰራቸውን ሲገልፁ ሌሎቹ ደግሞ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በተለያዩ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተፈጸሙ እስሮችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባን፣ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና የጸጥታ አካላት፣ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትን፣ ምስክሮችን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማነጋገር እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ ማቆያ ቦታዎችን በመጎብኘት ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ችግሯ መፈታቱን አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:30 0:00

XS
SM
MD
LG