በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት በኢትዮጵያ


የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ትግራይ ውስጥ በመንግሥቱ ቁጥጥር ሥር ወዳሉ እንዲሁም ከአማራና ከአፋር ክልሎች ጋር በሚዋሰኑ የትግራይ አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር እርምጃውን ማድነቃቸው የተነገረ ሲሆን የረድዔት ተቋማቱ እርዳታ ለማድረስ እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።

በአካባቢው ወደ 600 ሺህ የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሰው አጣዳፊ እርዳታ እንደሚያስፈልገውና በተደረሰው ስምምነት መሠረት ምግብ፣ መድኃኒቶችና ሌሎችም አቅርቦቶች እንደሚጓጓዙ ተነግሯል።

ትክክለኛ ቁጥር እስከአሁን ከየትናውም ወገን ባይወጣም በጦርነቱ ውስጥ በሺሆች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱ እየተነገረ ሲሆን 45 ሺህ የሚሆን ሰው ለስደት መዳረጉ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG