በአማራ ክልል በተለያየ ጊዜ ታስረው የነበሩ 13 ዳኞች ከእስር መለቀቃቸውን የክልሉ የዳኞች ማኅበር አስታወቀ። ዳኞቹ የተለቀቁት በተለያየ ጊዜ መኾኑን የተናገሩት፣ የማኅበሩ ተወካይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አሳሳ ፣ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ የቀሩት አምስት ዳኞች መለቀቃቸውን ተናግረዋል።
እያንዳንዱ ዳኛ በምን ምክንያት እንደታሰረ እና እንደተለቀቀ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የተናገሩት አቶ ብርሃኑ እንደ ማኅበር ግን ባለፈው ጥቅምት ወር 13 ዳኞች በሥራቸው ምክንያት መታሰራቸውን መግለጫ አውጥተው እንደነበር አስታውሰዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን እነሴ ሳር ምድር ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝደት የነበሩትና ለአራት ወራት ያህል ታስረው ባለፈው ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም የተለቀቁት አቶ ዘላለም ተመቸው በተጠረጠሩበት ወንጀን ታስረው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መለቀቃቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም