በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በካሎበዬይ


ካሎበዬይ በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አዲስ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ነዉ።

ካሎበዬይ በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አዲስ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ነዉ። በሀገሪቱ ከደዳብ ና ከካኩማ ቀጥሎ 3 ኛዉ የስደተኞች መጠለያ ሲሆን ካምፑ በ2015 በይፋ ሲከፈት በተለይ የደቡብ ሱዳን ቀዉስን ተከትሎ በቀጠናዉ ለተፈጠረዉ የሥደተኞች ቁጥር መናርን ከግምት በማስገባት ነበር።

ያ ብቻም ሳይሆን የደዳብ ሥደተኞች መጠለያ የወደፊት ዕጣም ፈንታን ከግምት በማስገባትም የተባበሩት መንግሥታት የዓለምቀፉ የሥደተኞች ጉዳይ የኬንያ ቅርንጫፍ ፈቃደኛ የሆኑትን ስደተኞች ወደ ካሎበዬይ ካምፕ በማዛወሩ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ካምፑ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች እንደ መጠጥ ውሃ እና ምግብ ያሉ አገልግሎቶች እጥረት እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት የኬንያ ቅርንጫፍ መ/ቤት ግን ካሎበዬይ ያሉ ስደተኞች ከሀገሪቱ ማኅበረሠብ ጋር የኢኮኖሚ ትስስር እንዲኖረው ዕቅድ እንደነበር ጠቅሶ ስደተኞች ስለሚያነሱት ስሞታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በካሎበዬይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG