በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት “ከሱዳኑ ጦርነት ይታደገን” ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዲመለሱ እየሠራ መኾኑን ገለጸ


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ

የሱዳኑ ጦርነት፣ የትግራይ ተወላጆች ወደተጠለሉባቸው መጠለያ ጣቢያዎች እየተቃረበ መኾኑን በመጥቀስ፣ በዚያ ያሉትን ስደተኞች እንዲታደግ የተጠየቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ መኾኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞቹን ሕይወት እንዲታደግ፣ ትላንት ረቡዕ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ጥሪ ያቀረቡት፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፌደራሉ መንግሥት የስደተኞቹ ሥቃይ እንዲያበቃ የሚችለውን ኹሉ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

በሱዳኑ ጦርነት መስፋፋት ችግር ላይ መውደቃቸውን የገለጹት ስደተኞቹም፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱላቸው ተማፅነዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ የአሜሪካ ድምፅ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ፣ የሱዳኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ፣ መንግሥት ዜጎችን የማስመለስ ሥራ እያከናወነ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG