በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሊቢያ እንዲወጡ የተደረጉ ፍልሰተኞች ጣሊያን ገቡ


ፍልስተኞቹ ፊውሚሲኖ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጓላቸዋል፤ ጣሊያን
ፍልስተኞቹ ፊውሚሲኖ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጓላቸዋል፤ ጣሊያን

የጣሊያን ባለሥልጣናት የተለያዩ አገር ዜግነት ያላቸውን 114 ፍልስተኞች በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ መስመሮች ፕሮጀክት ስም በሮም አቅራቢያ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ዛሬ ረቡዕ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፍልሰተኞቹ በዩኤንኤችሲአር የተመረጡ ሲሆን ከሊቢያ ትሪፖሊ እንዲወጡ የተደረጉ ናቸው፡፡

24 ሴቶችና ከአራት ዓመት በታች የሆኑ ስድስት ህጻናት የሚገኙበት ቡድን ውስጥ፣ ከሶሪያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሱዳን፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ከሶማሊያና ከኤርትራ የመጡ እንደሚገኙበት ተዘግቧል፡፡

የዩኤንኤችሲአር ተወካይ ቻይራ ካርዶሌቲ ፍልሰተኞቹ “ዕድለኞች ናቸው” በማለት ከ2 ሚሊዮን በላይ ከሚደርሱ ፍልሰተኞች መካከል በዚህ ዓመት ማውጣት የተቻለው 40 ሺዎችን ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በህገወጥ አስተላላፊዎች የሜዲትሬኒያንን ባህር አቋርጠው ጣሊያን መድረስ የቻሉት ፍልሰተኞች 90ሺ መሆናቸውን ሲነገር በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ መስመሮች ፕሮጀክት ስም መውጣት የቻሉት 500 ብቻ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በዩኤንኤችሲአር የሚመራ ሲሆን በጣሊያን መንግሥት፣ በቅዱስ ኤጊዲዮ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም በጣልያን ኢንቫጀሊካል ቤተክርስቲያናትና በዋልደኔሽያን ቤተክርስቲያን የገንዘብ ድጋፍ የሚታገዝ መሆኑን ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG