በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም የስደት ቁጥር አሻቅቧል


649 ጋዜጠኞች ተሰድደዋል፡፡

በቀደመው የአውሮፓዊያን 2010 ዓ.ም በመላው ዓለም ከመኖሪያው በኃይል የተፈናቀለው ሰው ቁጥር 43 ነጥብ 7 ሚሊየን እንደሚደርስ አንድ አዲስ የወጣ ሪፖርት አመለከተ፡፡

ዓመታዊ ዘገባውን ትናንት ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእነዚህ የየሃገሮች የውስጥ ተፈናቃዮችና ስደተኞች መካከል ሃያ አምስት ሺህ ለሚሆኑት ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ የሚደርሱባቸውን እሥራትና ሌሎችም ጥቃቶች በመሸሽ ቢያንስ 649 ጋዜጠኞች ወደሌሎች ሃገሮች ለመሰደድ መገደዳቸውን የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋቹ ዓለም አቀፍ ቡድን - ሲፒጄ አስታወቀ፡፡

ሲፒጄ ያስመረኮዘውን አዲስ ጥናት ይፋ ባደረገበት የዛሬ መግለጫው ጋዜጠኞች በብዛት ከሚሰደዱባቸው ሃገሮች ኢትዮጵያን በቀዳሚነት ጠቅሷል፡፡

ከጄኔቫ የዩኤንኤችሲአር ሪፖርት ይፋ ማድረጊያ ሥነ-ሥርዓት የደረሰንን የሊሣ ሽላይን ዘገባ እና የሲፒጂን ሪፖርት ጥንቅር ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG