በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፕሬዚዳንት የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ህግ መፈረማቸው ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ ኬንያ፣ ሶማሌ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘው ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ
ፎቶ ፋይል፦ ኬንያ፣ ሶማሌ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘው ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ህጉን መፈረማቸው ያስደሰተው መሆኑን ኢንተርናሽናል ሬስኪዩ ኮሚቴ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ።

ፕሬዚዳንቱ እርምጃውን መውሰዳቸው ኬንያ ውስጥ ለተጠለሉ ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ስደተኞች የትምህርት የሥራ እና ከኅበረተሰቡ ጋር የመዋሃድ ዕድል ይፈጥርላቸዋል ብሏል። የግብረ ሰናዩ ድርጅት የፖሊሲ አማካሪ ቪክተር ኦዴሮ ኬንያታ የዳዳብ እና ካኩማ ካምፖችን የሚዘጉበት የጊዜ ሰሌዳ ስድስት ወር በቀረው በአሁኑ ወቅት ህጉን መፈረማቸው ለስደተኞቹ ጉዳይ የመጨረሻ መፍትሄ ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

ሌላው ሬፊዩጂስ ኢንተርናሺናል የተባለው ድርጅት፣ ህጉ በኬንያ ያሉ ስደተኞች ጉዳይ የተቀናጀ መንግሥታዊ አሰራር ታቅዶለት ስደተኞቹ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያደርጋል ሲል በህጉ መፈረም ደስታውን ገልጻል።

XS
SM
MD
LG