አዲስ አበባ —
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ለአሜሪክ ድምጽ ሬድዮ እንደተናገሩት አገሪቱ ከ 700,000 በላይ ስደተኞችን በተለያዩ ካምፖች እያስተናገደች ነው።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን ከነዚህ አንዱ በሆነው አሶሳ አከባቢ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ሲከበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የጎረቤት ሃገሮች ስደተኞች ቁጥር እንዴት እየጨመር እንደመጣ ተመልክቷል።
የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ጋር የተካሄደው ቃለ-ምልልስ የመጀመርያ ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረ-እግዜብሄር ጋር የተካሄደው ቃለ-ምልልስ ሁለተኛ ክፍል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።