በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀይ መስቀል ወደ ዋግ ኽምራ የላከው ርዳታ መድረስ አልቻለም


ቀይ መስቀል ወደ ዋግ ኽምራ የላከው ርዳታ መድረስ አልቻለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

ቀይ መስቀል ወደ ዋግ ኽምራ የላከው ርዳታ መድረስ አልቻለም

በዐማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ፣ ድርቅ ባስከተለው ረኀብ ለተቸገሩ ዜጎች፣ የርዳታ እህል ለማድረስ አለመቻሉን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡

ከ400 ኩንታል በላይ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎቹ፣ ከመሀል ሀገር ወደ ክልሉ ቢገቡም፣ በግጭት መስፋፋት ሳቢያ ወደ ዞኑ ሳይደርሱ፣ በሞጣ እና ባሕር ዳር ከተሞች ላይ ለቀናት እንደቆሙ መኾናቸውን ማኅበሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ የሻምበል ዋለ፣ ቀይ መስቀል ተከታታይ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱን ቢያስታውቁም፣ አስተማማኝ የጸጥታ ኹኔታ ባለመኖሩ ርዳታው በየቦታው ለመቆም እንደተገደደ አመልክተዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ ሰሞኑን የዕቅድ አፈጻጸሙን በደብረ ማርቆስ ከተማ ሲገመግም፣ በኹሉም የጎጃም ዞኖች ያለው የሰላም ኹኔታ ከፍተኛ መሻሻሎች እንዳሳየ መግለጹ ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG