በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለምቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መግለጫ በኮቪድ-19


ፎቶ ፋይል፦ የጤና ሰራተኛ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት /አፍጋኒስታን/
ፎቶ ፋይል፦ የጤና ሰራተኛ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት /አፍጋኒስታን/

በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በታመሙ ሰዎችና እንክብካቤ በሚያደርጉላቸው የጤና ሰራተኞች ላይ በስፋት የጥቃት አድራጎት እየተፈፀመ መሆኑ የዓለምቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስገነዘበ።

አይሲአርሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ወረርሺኙ በዓለም ዙሪያ መዛመት በጀመረበት በየካቲት እና ባለፈው ሃምሌ ወር መካከል በነበረው ጊዜ በአርባ ሃገሮች በቫይረሱ ምክንያት በታመሙ ሰዎችና በህክምና ረዳቶቻቸው ላይ የደረሱ 611 ጥቃቶች መዝግበናል፤ ተጨባጩ ቁጥር ግን ከዚያ በእጅጉ እንደሚበልጥ እናምናለን ብለዋል።

ድብደባ፣ ስድብና የጥቃት ዛቻ ጨምሮ አብዛኛው ድርጊት የተመዘገበው በአፍጋኒስታን፣ ኮሎምቢያ እና ፊሊፒንስ መሆኑን ቀይ መስቀል ገልጿል።

የድርጊቱ መነሾ ፍርሃት እንደሆነ የገለፀው ድርጅቱ ቫይረሱ ይጋባብናል በሚል ፍርሃት የቤተሰብ አባል ሲሞት የሚከተለው ሃዘን እና በተለመደው መሰረት ቀብር ለማከናወን አለመቻሉ የሚፈጥረው ንዴት በምክንያትነት ጠቅሶታል።

XS
SM
MD
LG