በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን በአንድ ታጣቂ ቡድን ተጠልፈው የነበሩ የእርዳታ ሠራተኞች ተለቀቁ


ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በአንድ ታጣቂ ቡድን ተጠልፈው የነበሩ አሥር የእርዳታ ሠራተኞች መለቀቃቸውን ዓለምአቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በአንድ ታጣቂ ቡድን ተጠልፈው የነበሩ አሥር የእርዳታ ሠራተኞች መለቀቃቸውን ዓለምአቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።

አሥሩንም ደቡብ ሱዳናዊያን ሠራተኞች ዬዪ በምትባለው ከተማ አቅራቢያ ከሚገኝ ጣቢያ ወደ ዋና ከተማዪቱ ጁባ መውሰዱንም ኮሚቴው አመልክቷል።

የቀይ መስቀል ኮሚቴው በሁሉም ወገኖች ዕውቅና የማመላለሻ አገልግሎት ከመስጠቱ በስተቀር በድርድሮች ውስጥ አለመሣተፉንም ገልጿል።

አሥሩ የእርዳታ ሠራተኞች እርዳታ የሚያስፈልገውን ሰብዓዊ ሁኔታ ለመገምገም ባለፈው ረቡዕ ከዬዪ ከተማ ወደ ቶሬ አውራጃ እየተጓዙ ሳሉ እንደተጠለፉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ - ኦቻ አስታውቋል።

ሠራተኞቹ የኦቻ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት ፈንድ - ዩኒሴፍ፣ አክሮስ በሚል ምኅፃር የሚጠራው ክርስቲያን በጎ አድራጎት ለሱዳን፣ አክሽን አፍሪካ ኸልፕ፣ ፕላን ኢንተርናሽናልና የደቡብ ሱዳን የልማት ድርጅት የሚባሉ ተቋማት ባልደረቦች ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG