የዓለም ጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን በተረከቡ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ አገራቸውን ከተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት አባልነት ለማውጣት በደረሱበት ውሳኔ አዝነናል፣ “ዳግም ያጤኑታል የሚል እምነት አለን” ብሏል።
ትራምፕ አገራቸውን ካሁን ቀደም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዙ ደጋግመው ከተቹት የዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷን እንድትሰርዝ የሚል ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ሰነድ ፈርመዋል።
“ዩናይትድ ስቴትስ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምትከፍለው የገንዘብ መጠን ከቻይና ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው” ያሉት ትራምፕ የበዓለ ሲመታቸው ሥነ ስርዐት ከተከናወነ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ከዋይት ሀውስ በሰጡት አስተያየት “የዓለም ጤና ድርጅት ከመጠን በላይ የሆነ ገንዘብ በማስከፈል አጭበርብሮናል” ሲሉም አክለዋል።
ዋና መቀመጫውን በጄኔቫ ላደረገው የዓለም የጤና ድርጅት ዋናዋ ለጋሽ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም ጤና አጠባበቅ ሥራዎች ማስፈጸሚያ ወሳኝ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ ትሰጣለች።
መድረክ / ፎረም