በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ የደቡብ አፍሪካ አቻቸውን አነጋገሩ


ፎቶ ፋይል፦ ዋይት ሀውስ
ፎቶ ፋይል፦ ዋይት ሀውስ

የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪው ጄክ ሰለቨን እና የደቡብ አፍሪካ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ ሲድኒ ሙፋማዲን ትናንት ሰኞ ማነጋገራቸውን ከዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት የወጣው መግለጫ አመለከተ።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ፕሬዚዳንት ሲርል ራማፎሳ የሀገሮቻቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ሚስተር ሰለቨን እና ሚስተር ሙፋማዲ በድጋሚ ማረጋገጣቸውን መግለጫው አመልክቷል።

በቅርቡ በክዋዙሉ ናታል ክፍለ ሀገር በደረሰው ህይወት ያጠፋ የጎርፍ አደጋ ለተጎዳው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ እና መንግሥት ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንደምትሰጥ ሚስተር ሰልቨን ቃል ገብተውላቸዋል።

የዩክሬንን ቀውስ በሚመለከት ዩናይትድ ስቴትስ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁነቷን እንደምትቀጥል አጽንዖት ሰጥተው ገልጸውላቸዋል።

በተጨማሪም በንግድ፥ በኢንቬስትመንት፥ በጤና ጥበቃ ስርዓት እና ደህንነት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥን ዘርፎች አጋርነታችንን ለማጎልበት እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ በምታደርጋቸው ጸረ ሽብርተኛ እና በክልላዊ ጸጥታ ረገድ በምታደርጋቸው ጥረቶች ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪ ጄክ ሰልቨን አረጋግጠውላቸዋል።

የሩስያ የየክሬን ወረራ ባስቸኳይ መቆም እንዳለበት ያሰመሩበት ሚስተር ሰለቨን እና የደቡብ አፍሪካው አቻቸው ሲድኒ ሙፋማዲ ወረራው በአፍሪካ የአቅርቦት ሰንሰለት፣ የሸቀጥ ዋጋ እና የምግብ ዋስትና ላይ ያስከተለውን ጉዳት በሚመለከት የመፍትሄ ሃሳቦችን መለዋወጣቸውን መግለጫው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG