በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሥነ ግጥም ንባብ፥ ህትመትና ሥርጭት፤ ፈተናዎቹና መጪው ጊዜያት፤


የኢትዮጵያ ሥነ ፅሁፍ ዘመን የጠገበ ታሪካዊ መሠረት ቢኖረውም ያን ያህል ለማደግ ለመበልፀግ ግን አልታደለም። ጥበቡ ብቻ ሳይሆን ጥበበኛውም እንደተሰቃየ ነው፤ ለማለፍ የተገደደው፤ ይላሉ ተወያዮቹ። መፅሃፍት የማንበብ ልማድ፥ ህትመትና ስርጭት ውይይቱ የሚያተኩርባቸው አቢይ ነጥቦች ናቸው።

የዘመን ቀለማት ቁጥር ሁለት የግጥም ስብስብ ለውይይቱ መነሻ የሆነን መፅሃፍ ነው። መፅሃፉ ለህትመት የበቃው፥ ከግጥም መፅሃፋቸው ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ የግጥም ሥራዎቻቸውን የማሳተም ዕድል ያላገኙ ጀማሪ ገጣምያንን ሥራዎች ለህትመት ብርሃን ለማብቃት አስበው በተነሱ አንድ ገጣሚና በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ትብብር በተከፈተ ተዘዋዋሪ ሂሳብ አማካኝነት ነው።

በውጥኑ ሂደት፥ ከጅምሩ በገበይዋቸው ቁምነገሮችና ሌሎች ከምሳሌው ሊቀሰሙ በሚችሉ ቁም ነገሮች፤ ከዚህ ሻገር ብሎም፥ በመፅሃፍት የማንበብ ልማድ፥ እንዲሁም ህትመትና ስርጭትን በሚመለከቱ ሠፋ ያሉ ርዕሶች ዙሪያ ያጠነጠነ ውይይት ነው።

የውይይቱ ተካፋዮች፥ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በለጠና በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሎሳንጀለስ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ገጣሚው አቶ ሽመልስ አማረ ናቸው።

አቶ ሽመልስ አማረ ከወጣት ገጣሚያኑ ሥራ አንዱን በሚያነቡት ውይይቱ ይጀምራል።

XS
SM
MD
LG