በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋሚ የተፈናቀሉ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋሚ የተፈናቀሉ ከ37ሺህ በላይ ስዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ተከትሎ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን "ድጋሚ የተፈናቀለ የለም" ሲል አስተባበለ።

ከሳምንታት በፊት ከመተከል ጉባ ወረዳ ከተፈናቀሉ መካከልም 221 ሰዎች መመለሳቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ድጋሚ ተፈናቀሉ ያላቸውን አስመልክቶ የምዕራብ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት "ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋሚ ተፈናቅሎ በመጠለያ ውስጥ ያለ የለም" ካለ በኋላ "ባለፈው ዓመት ተፈናቅለው ወደ ክልሉ ያልተመለሱ በርካታ ሰዎች ግን የሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው" ብሏል።

"በድጋፍ ዕጦትና ፀጥታ ስጋት ድጋሚ ተፈናቀልን" ያሉ ግለሰቦች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋሚ የተፈናቀሉ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00


XS
SM
MD
LG